ይህንን እርዳታ ለማግኘት የሚከተሉትን ሦስት (3) ነገሮች ያድርጉ::
1. ምዝገባ ማከናወን-ይህን አስፈንጣሪ በመጫን ቪዲዮውን ይመልከቱና ጥያቄወችን ይመልሱ
2. እገዛውን ለማግኘት መስፈርቱን ማሟላትዎን ያረጋግጡ – አገልግሎቱን ለማግኘት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሆነው ካገኘንዎት
3. እገዛውን ማግኘት – መስፈርቱን ያሟሉ ሰዎች በሙሉ በመቀጠል ማድረግ ያለባቸውን መመሪያ የሚገልፅ ኢሜይል ወይንም የፁሁፍ መልክት እንዲደርሳቸው እናደርጋለን
በቂ ሰዎች እንደተመዘገቡ ምዝገባው ያቆማል
እያንዳንዱ ለዜግነት ማመልከት የሚፈልግ ግለሰብ የቅድሚያ ምዝገባ ማድረግ ይጠበቅበታል
- አንድ ምዝገባ ለአንድ ሰው ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የተመዘገቡ ሰዎች ተራቸውን ለሌላ ሰው አሳልፈው መስጠት አይችሉም
ቪዲዮና ጥያቄወች
እገዛውን ለማግኘት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሆነው ካገኘንዎት በኢምግሬሺን ጠበቃዎችና የሃገሪቱ የፍትህ ሚንስትር ፈቃድ ባላቸው ተወካዮች ድጋፍ ያገኛሉ የሚያገኙት የህግ አገልግሎት ያለ ምንም ክፍያ በነፃ የሚቀርብ ሲሆን የሚያቀርቡት መረጃወች በሙሉ በሚስጥር የሚያዙ ይሆናል::
ባለብን የቦታ ውስንነትና በኮቪድ 19 ተዋህሲ ምክንያት ሁሉም ተመዝጋቢ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናል ብለን ቃል አንገባም::
ስለ ታጋሺነትዎ ትብብረዎና አስተዋይነትዎ ልባዊ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡
ከታላቅ አክብሮት ጋር
የአዲስ ዜጋ ፕሮጀክት
PROJECT NEW CITIZEN
Recent Comments