ይህንን እርዳታ ለማግኘት የሚከተሉትን ሦስት (3) ነገሮች ያድርጉ::
1.ምዝገባ ማከናወን-ይህን አስፈንጣሪ በመጫን ቪዲዮውን ይመልከቱና ጥያቄወችን ይመልሱ
2.እገዛውን ለማግኘት መስፈርቱን ማሟላትዎን ማረጋገጥ– መልስዎን ተመልክተን አገልግሎቱን ለማግኘት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሆነው ካገኘንዎ እንደውልለዎታለን
3.እገዛውን ማግኘት- ከሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ. ም. (May 17,2021) ጀምሮ ቀጠሮ እንዲይዙ ደውለን እናናግርዎታለን
* ቢያንስ ሁለት ጊዜ ደውለን ለማግኘት እንሞክራለን
ቪዲዮና ጥያቄወች
እገዛውን ለማግኘት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሆነው ካገኘንዎት በኢምግሬሺን ጠበቃዎችና የሃገሪቱ የፍትህ ሚንስትር ፈቃድ ባላቸው ተወካዮች ድጋፍ ያገኛሉ የሚያገኙት የህግ አገልግሎት ያለ ምንም ክፍያ በነፃ የሚቀርብ ሲሆን የሚያቀርቡት መረጃወች በሙሉ በሚስጥር የሚያዙ ይሆናል::
ባለብን የቦታ ውስንነትና በኮቪድ 19 ተዋህሲ ምክንያት ሁሉም ተመዝጋቢ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናል ብለን ቃል አንገባም::
ስለ ታጋሺነትዎ ትብብረዎና አስተዋይነትዎ ልባዊ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡
ከታላቅ አክብሮት ጋር
የአዲስ ዜጋ ፕሮጀክት
PROJECT NEW CITIZEN
Recent Comments